Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 10:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የኖኅ የል​ጆቹ ነገ​ዶች እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሕዝ​ቦች በም​ድር ላይ ተዘሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች፥ እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ሁሉም የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኍላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተክከፋፈሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 10:32
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድር ሁሉ ላይ የተ​በ​ተኑ የኖኅ ልጆች እነ​ዚህ ሦስቱ ናቸው።


እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው።


የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካ​ምና፥ የያ​ፌት ትው​ልድ ይህ ነው፤ ከጥ​ፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው።


ለዔ​ቦ​ርም ሁለት ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘ​መኑ ተከ​ፍ​ላ​ለ​ችና፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ዮቅ​ጣን ነው።


የካም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።


እና​ን​ተም ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።


የሴም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።


የዓ​ለም ሁሉ ቋንቋ አንድ፥ ንግ​ግ​ሩም አንድ ነበረ።


ከእ​ነ​ዚ​ህም የአ​ሕ​ዛብ ደሴ​ቶች ሁሉ በየ​ም​ድ​ራ​ቸው፥ በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ተከ​ፋ​ፈሉ።


ምድር ለእ​ነ​ርሱ ብቻ ተሰ​ጥ​ታ​ለ​ችና፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እን​ግዳ ሕዝብ አል​ገ​ባ​ባ​ቸ​ው​ምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች