Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ብር​ሃን ይሁን” አለ፤ ብር​ሃ​ንም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:3
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።


ብር​ሃ​ንም በጨ​ለማ ያበ​ራል፤ ጨለ​ማም አላ​ገ​ኘ​ውም።


ብር​ሃ​ንን ፈጠ​ርሁ፤ ጨለ​ማ​ው​ንም ፈጠ​ርሁ፤ ሰላ​ም​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፋ​ት​ንም አመ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ያደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።


ፀሐይ በቀን የሚ​ያ​በ​ራ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ በሌ​ሊ​ትም ጨረቃ የሚ​ወ​ጣ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ ለአ​ን​ቺስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ፥ አም​ላ​ክ​ሽም ክብ​ርሽ ይሆ​ናል።


ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።


ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።


ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው።


ፍር​ዱም ይህ ነው፤ ብር​ሃን ወደ ዓለም መጥ​ቶ​አ​ልና፤ ሰውም ሥራው ክፉ ስለ​ሆነ ከብ​ር​ሃን ይልቅ ጨለ​ማን መር​ጦ​አ​ልና።


ይህ ችግ​ረኛ ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፥ ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። እርሱ ብሎ​አ​ልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዝ​ዞ​አ​ልና፥ ተፈ​ጠሩ፤


ለሚ​ፈ​ሩት ችግር የለ​ባ​ቸ​ው​ምና ቅዱ​ሳን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት።


ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል።


“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።


ተቀ​ኙ​ለት፥ ዘም​ሩ​ለት፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም ሁሉ ተና​ገሩ።


“የብ​ር​ሃን ማደ​ር​ያው ቦታ የት ነው? የጨ​ለ​ማስ ቦታው ወዴት አለ?


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።


እነሆ፥ በዙ​ሪ​ያው ብር​ሃ​ኑን ይዘ​ረ​ጋል የባ​ሕ​ሩ​ንም ጥል​ቀት ይከ​ድ​ነ​ዋል።


ይህ​ንም ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸና፥ “አል​ዓ​ዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ።


እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን፥ በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ፍጥ​ረት ይህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች