Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ምድር ሕያ​ዋን ፍጥ​ረ​ታ​ትን እንደ ወገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችን፥ የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ ታውጣ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶችን፥ እንደየዐይነታቸው እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና አራዊትን እንደየዐይነታቸው ታስገኝ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:24
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እነሆ፥ በአ​ንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበ​ላል።


ከወ​ፎች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከእ​ን​ስ​ሳም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ሳቡ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከአ​ንተ ጋር ይመ​ገቡ ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወን​ድና ሴት እየ​ሆኑ ወደ አንተ ይግቡ።


አራ​ዊት ሁሉ፥ እን​ስ​ሳም ሁሉ፥ ወፎ​ችም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከመ​ር​ከብ ወጡ።


አራ​ዊ​ትም፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ፥ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም፥ የሚ​በ​ርሩ ወፎ​ችም፤


“የሜ​ዳ​ው​ንስ አህያ ነጻ​ነት ማን አወ​ጣው? ከእ​ስ​ራ​ቱስ ማን ፈታው?


አራ​ዊ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ወፎ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ የሚ​በሩ ወፎ​ችም ሁሉ፥


እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ ግብፅ ገባ፥ ያዕ​ቆ​ብም በካም ምድር ተቀ​መጠ።


እግ​ሮ​ቹም በእ​ግር ብረት ሰለ​ሰሉ፥ ሰው​ነ​ቱም ከብ​ረት አመ​ለ​ጠች።


“ለፈ​ረስ አንተ ጕል​በ​ቱን ሰጥ​ተ​ኸ​ዋ​ልን? አን​ገ​ቱ​ንስ ጋማ አል​ብ​ሰ​ኸ​ዋ​ልን?


“ጎሽ ያገ​ለ​ግ​ልህ ዘንድ ይፈ​ቅ​ዳ​ልን? ወይስ በግ​ር​ግ​ምህ አጠ​ገብ ያድ​ራ​ልን?


“ዋልያ የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ትን ጊዜ ታው​ቃ​ለ​ህን? የም​ታ​ም​ጥ​በ​ት​ንስ ጊዜ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለ​ህን?


ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አም​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንና የሰ​ማይ ወፎ​ችን ሁሉ ደግሞ ከም​ድር ፈጠረ፤ በምን ስም እን​ደ​ሚ​ጠ​ራ​ቸ​ውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመ​ጣ​ቸው፤ አዳ​ምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እን​ደ​ጠ​ራው ስሙ ያው ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች