Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ታላ​ቅና ብዙ ሆነ​ዋል፤ ከእ​ኛም ይልቅ በር​ት​ተ​ዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፤ እስራኤላውያን በቍጥር በልጠውናል፤ ከእኛም ይልቅ እየበረቱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ እነዚህ እስራኤላውያን ቊጥራቸው በዝቶአል፤ የኀይላቸውም ብርታት አስጊ ሆኖብናል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርሱም ሕዝቡን፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 1:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን፥ “ከእኛ ተለ​ይ​ተህ ሂድ፤ ከእኛ ይልቅ እጅግ በር​ት​ተ​ሃ​ልና” አለው።


አለ​ውም፥ “የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መው​ረ​ድን አት​ፍራ፤ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለ​ሁና።


ሰነ​ፉን ሰው ቍጣ ይገ​ድ​ለ​ዋ​ልና፥ ቅን​ዓ​ትም ሰነ​ፉን ያጠ​ፋ​ዋል።


ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ አለ፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ በም​ድር በጣም በዝ​ተ​ዋል፤ እና​ን​ተም ከሥ​ራ​ቸው አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ቸ​ዋል።


የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።


እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።


ወይስ መጽሐፍ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፤” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች