Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚ​ህም በክፉ ቀን መቃ​ወም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ያዙ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ኑም በሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጃ​ችሁ ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ክፉው ቀን ሲመጣ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ፤ ሁሉን ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን የጦር ትጥቅ አንሡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ በክፉ ቀን የጠላትን ኀይል ለመቋቋም እንድትችሉና ሁሉንም ፈጽማችሁ ጸንታችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር መሣሪያ አንሡ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 6:13
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጭ​ን​ቀት ቀን ሳይ​መጣ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ወራት ፈጣ​ሪ​ህን ዐስብ፤ ደስ አያ​ሰ​ኙም የም​ት​ላ​ቸው ዓመ​ታት ሳይ​ደ​ርሱ፥


ክፉ ቀንን ለሚ​ፈ​ል​ጓት፥ የሐ​ሰት ሰን​በ​ታ​ትን ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ር​ቡና አንድ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥


ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?


እን​ግ​ዲህ ከዚህ ከሚ​መ​ጣው ሁሉ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ማም​ለጥ እን​ድ​ት​ችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እን​ድ​ት​ቆሙ ሁል​ጊዜ ትጉ።”


በጭ​ን​ጫም ላይ የወ​ደ​ቀው ሰም​ተው ነገ​ሩን በደ​ስታ የሚ​ቀ​በ​ሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊ​ዜው ያም​ናሉ እንጂ ሥር የላ​ቸ​ውም፤ መከ​ራም በአ​ገ​ኛ​ቸው ጊዜ ይክ​ዳሉ።


ሌሊቱ አል​ፎ​አል፤ ቀኑም ቀር​ቦ​አል። እን​ግ​ዲህ የጨ​ለ​ማን ሥራ ከእና እና​ርቅ፤ የብ​ር​ሃ​ን​ንም ጋሻ ጦር እን​ል​በስ።


የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ።


ቀኖች ክፉ​ዎች ናቸ​ውና ዘመ​ኑን ዋጁት።


በከ​ንቱ ነገ​ርም የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ አይ​ኑር፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት በከ​ሓ​ዲ​ዎች ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ይመ​ጣ​ልና።


ከእ​ና​ንተ ወገን የሚ​ሆን ኤጳ​ፍ​ራ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል፥ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ወ​ደው ነገር ሁሉ ምሉ​ኣ​ንና ፍጹ​ማን እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ስለ እና​ንተ ዘወ​ትር ይጸ​ል​ያል፤ ይማ​ል​ዳ​ልም።


እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤


ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፤ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኀጢአትን ትቶአልና።


የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።


ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች