Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢ​አ​ተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ በክ​ር​ስ​ቶስ መን​ግ​ሥት ዕድል ፋንታ እን​ደ​ሌ​ለው ይህን ዕወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ደግሞም ይህን ዕወቁ፤ ማንም አመንዝራ ወይም ርኩስ ወይም ስግብግብ፣ ይኸውም ጣዖት አምላኪ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኩስ ወይም ስስታም ማለትም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አመንዝራም ቢሆን፥ ማናቸውንም የርኲሰት ሥራ የሚያደርግ ቢሆን፥ ወይም ጣዖት እንደ ማምለክ የሆነ ስግብግብነት ቢሆን፥ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማያገኝ ዕወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 5:5
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም።


ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


ምድ​ራዊ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ከዝ​ሙ​ትና ከር​ኵ​ሰት፥ ከጥ​ፋ​ትና ከክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማም​ለክ ከሆ​ነው ከቅ​ሚ​ያም ግደ​ሉት።


ነገር ግን ለቅ​ዱ​ሳን እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው፥ ዝሙ​ትና ርኵ​ሰት ሁሉ ወይም ቅሚያ አይ​ሰ​ማ​ባ​ችሁ።


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


የሥ​ጋም ሥራው ይታ​ወ​ቃል፤ እር​ሱም ዝሙት፥ ርኵ​ሰት፥ መዳ​ራት፥


መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ቤት አት​መኝ፤ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከብ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማን​ኛ​ው​ንም አት​መኝ።”


በዘ​ረፋ መካ​ከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛ​ኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመ​ኘ​ኋ​ቸው፤ ወሰ​ድ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ሆም በድ​ን​ኳኔ ውስጥ በመ​ሬት ተሸ​ሽ​ገ​ዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።


በዚህ ነገር ዕድ​ልና ርስት የለ​ህም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብህ የቀና አይ​ደ​ለ​ምና።


አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ሊያ​ን​ጻ​ችሁ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም ሁሉ መካ​ከል ርስ​ትን ሊሰ​ጣ​ችሁ ለሚ​ች​ለው ለጸ​ጋው ቃል አደራ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ።


ከጨ​ለማ አገ​ዛዝ አዳ​ነን፤ ወደ ተወ​ደ​ደው ልጁ መን​ግ​ሥ​ትም መለ​ሰን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች