Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይቅር ስላ​ለን የጸ​ጋ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነት ብዛት በሚ​መ​ጣው ዓለም ይገ​ልጥ ዘንድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይኸውም በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልንን ወደር የሌለውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ይኸውም በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት መለኪያ የሌለውን የጸጋውን ባለጠግነት ሊያሳይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህንንም ያደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የገለጠውን ቸርነትና ወደር የሌለውን የጸጋውን ብልጽግና በሚመጡት ዘመናት ሊያሳየን ብሎ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 2:7
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ሕ​ረቱ ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና በወ​ደ​ደን በፍ​ቅሩ ብዛት፥


የተ​ተ​ው​ሽና የተ​ጠ​ላሽ ሆነ​ሻ​ልና የሚ​ረ​ዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታን ለልጅ ልጅ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ።


በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያል​ተ​ገ​ለጠ ዛሬ ለቅ​ዱ​ሳን ሐዋ​ር​ያ​ቱና ለነ​ቢ​ያቱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እንደ ተገ​ለጠ፥


ለእ​ርሱ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ በት​ው​ልድ ሁሉ ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?


በእ​ር​ሱም እንደ ቸር​ነቱ ብዛት በደሙ ድኅ​ነ​ትን አገ​ኘን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ተሰ​ረ​የ​ልን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች