Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉት አሕ​ዛብ የሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት አትከተል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዙሪያህ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ የሚሰግዱላቸውን ሌሎችን ባዕዳን አማልክት አታምልኩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14-15 በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና የአምላክህ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዳይነድድብህ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ፥ በዙሪያችሁ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 6:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ አት​ሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውም።


“ከእኔ በቀር ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አታ​ም​ልክ።


ትገ​ዙ​ላ​ቸ​ውና ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ክፉም እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ አታ​ስ​ቈ​ጡኝ።


ደግ​ሞም፦ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ሥራ​ች​ሁ​ንም አሳ​ምሩ፤ ታገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ሁት ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ እያ​ልሁ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ልኬ​ባ​ችሁ ነበር፤ እና​ንተ ግን ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።


መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ባት​ገፉ፥ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታ​ፈ​ስሱ፥ ክፉም ሊሆ​ን​ባ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተሉ፤


መር​ገ​ምም፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ባት​ሰሙ፥ ዛሬ ካዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የማ​ታ​ው​ቁ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ፥ ብታ​መ​ል​ኳ​ቸ​ውም ነው።


ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀ​ረ​ቡት ከአ​ን​ተም የራ​ቁት አን​ተን ከብ​በ​ውህ ያሉ አሕ​ዛብ ከሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸው አማ​ል​ክት፥


“ከእኔ በቀር ሌሎች አማ​ል​ክት አይ​ሁ​ኑ​ልህ።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።


በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤


ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች