Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ያል​ሞ​ላ​ሃ​ቸ​ው​ንም ሀብ​ትን የሞሉ ቤቶች፥ ያል​ማ​ስ​ሃ​ቸ​ው​ንም የተ​ማሱ ጕድ​ጓ​ዶች፥ ያል​ተ​ከ​ል​ሃ​ቸ​ው​ንም ወይ​ንና ወይራ በሰ​ጠህ ጊዜ፥ በበ​ላ​ህና በጠ​ገ​ብ​ህም ጊዜ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የራስህ ባልነበሩ መልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶችን፣ ያልቈፈርሃቸውን የውሃ ጕድጓዶች፣ ያልተከልሃቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ሲሰጥህና በልተህም ስትጠግብ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልቆፈርካቸውም የተቆፈሩ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም የወይን ተክልና የወይራ ዛፎች፥ ስትበላና ስትጠግብ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የምትወርሳቸው ቤቶች አንተ ባላኖርከው መልካም ነገር የተሞሉ ይሆናሉ፤ ያልቈፈርካቸውም የውሃ ጒድጓዶች በዚያ ይገኛሉ፤ እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸው የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ይገኛሉ፤ እግዚአብሔር ወደዚህች ምድር አስገብቶህ በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጉድጉዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 6:11
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምሽ​ጎ​ቹ​ንም ከተ​ሞች፥ መል​ካ​ምን ነገር የሞ​ሉ​ትን ቤቶች፥ የተ​ማ​ሱ​ት​ንም ጕድ​ጓ​ዶች፥ የወ​ይ​ኖ​ቹ​ንና የወ​ይ​ራ​ዎ​ቹን ቦታ​ዎች፥ ብዙ​ዎ​ቹ​ንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገ​ቡም፤ ወፈ​ሩም፤ በታ​ላቅ በጎ​ነ​ት​ህም ደስ አላ​ቸው።


እንደ ተጨ​ነ​ቁም ተመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰማ​ቸው፤


በሜ​ዳህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ችህ ሣርን ይሰ​ጣል፤ ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ።


ሌዋ​ዊ​ዉም፥ ከአ​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት የለ​ው​ምና፥ በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግም፥ መበ​ለ​ትም መጥ​ተው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ታ​ደ​ር​ገው በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ነው።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ራ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጥ​ህን አሕ​ዛብ ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥


ያዕ​ቆብ በላ፤ ጠገ​በም፤ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን ጥጋብ አቀ​ና​ጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ተወ፤ ከሕ​ይ​ወቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራቀ።


ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ት​ንም ምድር፥ ያል​ሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውም፤ ካል​ተ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከወ​ይ​ንና ከወ​ይራ በላ​ችሁ።’


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች