Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ስለዚህም ለሮቤል ነገድ ከፍታ ባለው በረሓ የምትገኘው የቤጼር ከተማ፥ ለጋድ ነገድ በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞትና፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ግዛት ውስጥ የምትገኘው ጎላን እንዲለዩ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:43
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


ለሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከሮ​ቤል ነገድ፥ ከጋ​ድም ነገድ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰጡ።


ከቀ​ዓ​ትም ልጆች ወገ​ኖች ለአ​ን​ዳ​ን​ዶቹ ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ ከተ​ሞች ድርሻ ነበ​ራ​ቸው።


ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ወገን በባ​ሳን ያለ​ችው ጋው​ሎ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ አስ​ታ​ሮ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤


ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ​ችው ሬማ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ መሃ​ና​ይ​ምና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤


ትና​ንት፥ ከት​ናት በስ​ቲ​ያም ጠላቱ ያል​ሆ​ነ​ውን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ገዳዩ ይማ​ፀ​ን​ባ​ቸው ዘንድ፥ ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ፅኖ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ፤


ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ያኖ​ራት ሕግ ይህች ናት፤


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።


ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገ​ኖች ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ በባ​ሳን ውስጥ የሆ​ነ​ች​ውን ጎላ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ከሮ​ቤል ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ በሚ​ሶን ምድረ በዳ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች