Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግ​ብፅ ከአ​ንተ የጸ​ኑ​ትን ታላ​ላ​ቆ​ቹን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አን​ተ​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ባህ፥ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ርስት አድ​ርጎ እን​ዲ​ሰ​ጥህ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ይህንንም ማድረጉ ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ከእናንተ የሚበልጡትንና ኀያላን የሆኑትን ሕዝቦች አስወጥቶ ምድራቸውን ለእናንተ ርስት ለማድረግ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:38
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ አሁን ለወ​ሮ​ታ​ችን ክፋት ይመ​ል​ሱ​ል​ናል፤ ከሰ​ጠ​ኸ​ንም ርስት ያወ​ጡን ዘንድ መጥ​ተ​ዋል።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነ​በ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ከሕ​ዝ​ብህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ያሳ​ደ​ድህ፥ ለወ​ዳ​ጅ​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም ዘር ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰ​ጠ​ሃት አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የሰ​ጣት ምድር የከ​ብት መሰ​ማ​ሪያ ሀገር ናት፤ ለእ​ኛም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ብዙ እን​ስ​ሳት አሉን።


የሮ​ቤ​ልም ልጆች ነገድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት፥ የጋ​ድም ልጆች ነገድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስ​ታ​ቸ​ውን ወር​ሰ​ዋል።


እነ​ዚህ ሁለቱ ነገ​ድና የአ​ንዱ ነገድ እኩ​ሌታ ርስ​ታ​ቸ​ውን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወረሱ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያወ​ጣል፤ ከእ​ና​ን​ተም የሚ​በ​ል​ጡ​ትን፥ የሚ​በ​ረ​ቱ​ት​ንም አሕ​ዛብ ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ አሞ​ራ​ዊ​ውን ሴዎ​ን​ንና ምድ​ሩን በፊ​ትህ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ መስ​ጠት እነሆ፥ ጀመ​ርሁ፤ ምድ​ሩን ትገዛ ዘንድ መው​ረስ ጀምር’ አለኝ።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት ወደ​ም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ባመ​ጣህ ጊዜ፥ ከፊ​ት​ህም ብዙና ታላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን፥ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ትን፥ የበ​ረ​ቱ​ት​ንም ሰባ​ቱን አሕ​ዛብ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ባወጣ ጊዜ፥


ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው።


ኢያ​ሱም አለ፥ “ሕያው አም​ላክ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ፥ እር​ሱም ከፊ​ታ​ችሁ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ፈጽሞ እን​ዲ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በዚህ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች