Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ይህ ነገር ሕይ​ወ​ታ​ችሁ ነው እንጂ ለእ​ና​ንተ ከንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ በዚ​ህም ነገር ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ዘመ​ና​ችሁ ይረ​ዝ​ማል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃሎች አይደሉም፤ በእነርሱ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፣ በምትወርሷትም ምድር ረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ይህ ነገር ለእናንተ ሕይወታችሁ ነው እንጂ ከንቱ ነገር አይደለም። በዚህም ነገር ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ይህ ሕግ የባዶ ቃላት ቅንብር አይደለም፤ እርሱ የሕይወታችሁ መሠረት ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ቃል ታዛዦች ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር ለረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ረጅም ዘመን ትቀመጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:47
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።


ነፍስህ ትድን ዘንድ፥ ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ። ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።


ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።


ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና።


በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እኔን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


በም​ድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ መካ​ከል የነ​በረ እርሱ ነው፤ በደ​ብረ ሲና ከአ​ነ​ጋ​ገ​ረው መል​አ​ክና፤ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ጋር ለእኛ ሊሰ​ጠን የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል የተ​ቀ​በለ እርሱ ነው።


ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዛት ብት​ሰማ፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብት​ወ​ድድ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም ሁሉ ብት​ሄድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ብት​ጠ​ብቅ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ፤ በቍ​ጥ​ርም ትበ​ዛ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ሄ​ድ​ባት በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።


የማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ሄ​ዱ​ባት ምድር በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይስሙ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ይማሩ።”


ጫማህ ብረ​ትና ናስ ይሆ​ናል፤ እንደ ዕድ​ሜህ እን​ዲሁ ኀይ​ልህ ይሆ​ናል።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


ጠብ​ቁት፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ ይህን ሥር​ዐት ሁሉ ሰም​ተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢ​ብና አስ​ተ​ዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአ​ሕ​ዛብ ፊት ጥበ​ባ​ች​ሁና ማስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ ይህ ነውና፤


ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች