Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በም​ድር ኀይል ላይ አወ​ጣ​ቸው፤ የእ​ር​ሻ​ው​ንም ፍሬ መገ​ባ​ቸው፤ ከዓ​ለ​ትም ድን​ጋይ በሚ​ገኝ ማር፥ ከጭ​ን​ጫ​ውም ድን​ጋይ በሚ​ገኝ ዘይት አሳ​ደ​ጋ​ቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የዕርሻንም ፍሬ መገበው። ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፥ የምድሩንም ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ ማር፥ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “በከፍተኛ ቦታ ላይ አኖረው፤ የምድሩንም ምርት መገበው፤ ከቋጥኝ የተገኘውን ማርና ከድንጋያማ መሬት ከበቀለው ወይራ የተገኘውን ዘይት መገበው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የእርሻውን ፍሬ በላ፤ 2 ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ 2 ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:13
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ሮቼን እንደ ዋልያ እግ​ሮች አጸና፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም አቆ​መኝ።


የመ​ን​ጋ​ዎ​ቹ​ንም ጥጆች፥ የማ​ሩ​ንና የቅ​ቤ​ው​ንም ፈሳሽ አይ​መ​ለ​ከ​ትም።


ቅቤ በመ​ን​ገዴ ይፈ​ስስ በነ​በረ ጊዜ፥ ወተት በተ​ራ​ራዬ ይፈ​ስ​ስ​ልኝ በነ​በረ ጊዜ።


በም​ድረ በዳም በተ​ጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓ​ለቱ ውስጥ ያፈ​ል​ቅ​ላ​ቸው ነበር፤ ዓለ​ቱም ተሰ​ነ​ጠቀ፤ ውኃ​ውም ይፈ​ስ​ስ​ላ​ቸው ነበር፤ ሕዝ​ቤም ይጠጡ ነበር።


በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትታ​መ​ና​ለህ፤ በም​ድ​ርም በረ​ከት ላይ ያወ​ጣ​ሃል፤ የአ​ባ​ትህ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ርስት ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ደ​ዚህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


በወ​ር​ቅና በብር አጌ​ጥሽ፤ ልብ​ስ​ሽም ጥሩ በፍ​ታና ሐር፥ ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አን​ቺም መል​ካ​ምን ዱቄ​ትና ማርን፥ ዘይ​ት​ንም በላሽ፤ ወፈ​ርሽ፤ እጅ​ግም ውብ ሆንሽ፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀሽ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።


እኔ ደግሞ እጄን በእጄ ላይ አጨ​በ​ጭ​ባ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም እል​ካ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጠላት በእ​ና​ንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጥፋት፥ ለእኛ ርስት ሆነ​ዋል ብሎ​አ​ልና፤


ከተ​ሰ​ማ​ራ​ችሁ በኋላ ጠገ​ባ​ችሁ፤ በጠ​ገ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ልባ​ችሁ ታበየ፤ ስለ​ዚ​ህም ረሳ​ች​ሁኝ።


“ሁሉን አብ​ዝቶ ስለ ሰጠህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ሥ​ሓና በቀና ልብ አላ​መ​ለ​ክ​ኸ​ው​ምና፥


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”


የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥


ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች