Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 28:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 ከአ​ካ​ልዋ የሚ​ወ​ጣ​ውን የእ​ን​ግዴ ልጅ፥ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸ​ው​ንም ልጆች፤ በደ​ጆ​ችህ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ፤ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሁሉን ስላ​ጣች በስ​ውር ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 ከማሕፀኗ የወጣውን እንግዴ ልጇንና የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ ይህን የምታደርገውም በመከራው ወቅት ጠላቶችህ ከተሞችህን ከብበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፣ እነርሱን ደብቃ ለመብላት ስትል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 ከማሕፀኗ የወጣውን እንግዴ ልጅንና የምትወልዳቸውን ልጆች ትጠየፋለች፤ ይህን የምታደርገውም በመከራው ወቅት ጠላቶችህ ከተሞችህን ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ እነርሱን ተደብቃ ለመብላት ስትል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው፥ በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው የጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላ ነገር ስለሌላት በምሥጢር ከምትበላቸው ከማሕፀንዋ ከወጡ ልጆችዋና ከእንግዴልጅዋ ለማንም አትሰጥም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 በወንድና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች፤ በደጆችህም ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሁሉን ስላጣች በስውር ትበላቸዋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 28:57
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እን​በ​ላ​ለን አለ​ችኝ።


ልጄ​ንም ቀቅ​ለን በላ​ነው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም፦ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ አል​ኋት፤ ልጅ​ዋ​ንም ሸሸ​ገ​ችው” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት።


“በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም።


ዮድ። የር​ኅ​ሩ​ኆች ሴቶች እጆች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ቀቅ​ለ​ዋል፤ የወ​ገኔ ሴት ልጅ በመ​ቀ​ጥ​ቀ​ጥዋ መብል ሆኖ​አ​ቸው።


ጠላ​ቶ​ች​ህም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ሥጋ ትበ​ላ​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች