Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በኀ​ዘ​ኔም ጊዜ እኔ ከእ​ርሱ አል​በ​ላ​ሁም፤ ለር​ኩ​ስም ነገር ከእ​ርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አል​ሠ​ዋ​ሁም፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች ለሞተ ሰው አል​ሰ​ጠ​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ኬ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ኝ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በሐዘን ላይ ሳለሁ፣ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚሁ ላይ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም፤ አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በኀዘኔም ጊዜ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ወይም ንጹህ ባልነበርኩ ጊዜ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት መባ የለም፤ ለአምላኬ ጌታ ድምጽ ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሞት ሐዘን ጊዜ ከእርሱ አልበላሁም፤ ንጹሕ ባልሆንኩበት ጊዜ ከእርሱ ምንም አላነሣሁም፤ ስለ ሞተ ሰው ለሚቀርብ መባ ከእርሱ ምንም አላቀረብኩም፤ ባዘዝከኝ መሠረት የአንተን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በኅዘኔ ጊዜ እኔ ከእርሱ አልበላሁም፥ ለርኩስነቴም ከእርሱ አላወጣሁም፥ ከእርሱም አንዳች ለሞተ ሰው አልሰጠሁም፤ የአምላኬንም የእግዚአሔርን ቃል ሰምቼአለሁ፥ ያዘዝኽኝንም ሁሉ አድርጌአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 26:14
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።


ሰዎ​ችም ስለ ሞቱት ለማ​ጽ​ና​ናት የእ​ዝን እን​ጀራ አይ​ቈ​ር​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ አባ​ታ​ቸ​ውና ስለ እና​ታ​ቸ​ውም የመ​ጽ​ና​ናት ጽዋ አያ​ጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም።


በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ይን ጠጅን ቍር​ባን አያ​ቀ​ር​ቡም፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ውም፤ እንደ ኀዘ​ንም እን​ጀራ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ይረ​ክ​ሳል፤ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውም ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ይሆ​ናል እንጂ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ገ​ባም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፥ “ከወ​ገ​ና​ቸው በሞተ ሰው ራሳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለካ​ህ​ናቱ ለአ​ሮን ልጆች ንገ​ራ​ቸው።


ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይ​ግባ፤ በአ​ባ​ቱም ወይም በእ​ናቱ አይ​ር​ከስ።


ኀጢ​አት ሳለ​ባት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ የበ​ላች ሰው​ነት፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።


ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፣ እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ታደ​ር​ጋ​ትም ዘንድ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥


አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያሉ መጻ​ተ​ኛና ድሃ-አደግ፥ መበ​ለ​ትም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በሚ​መ​ር​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ በል፦ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር ከቤቴ ለይች ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሀ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ ትእ​ዛዝ ሁሉ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ምንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ሁም፤ አል​ረ​ሳ​ሁ​ምም፤


ከቅ​ዱስ ማደ​ር​ያህ ከሰ​ማይ ጐብኝ፤ ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን፥ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ትሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን እንደ ማል​ህ​ላ​ቸው የሰ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ንም ምድር ባርክ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች