Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “አባ​ቶች ስለ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በኀ​ጢ​አቱ ይገ​ደል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፥ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “ልጆቻቸው በሠሩት ወንጀል ወላጆች በሞት መቀጣት የለባቸውም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ወንጀል ልጆቻቸው በሞት አይቀጡ፤ እያንዳንዱ ሰው በሠራው ወንጀል በሞት ይቀጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 24:16
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች በል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ችም በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፋንታ አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ግን አል​ገ​ደ​ለም።


ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።


እነሆ ነፍ​ሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአ​ባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እን​ዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢ​አት የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች።


የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም።


ንጉ​ሡም፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ሆይ! አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች