Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወን​ድ​ም​ህም በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያህ ባይ​ሆን ወይም ባታ​ው​ቀው ይዘ​ሃ​ቸው ወደ ቤትህ ትገ​ባ​ለህ፤ ወን​ድ​ምህ እስ​ኪ​ሻ​ቸው ድረስ በአ​ንተ ዘንድ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ለእ​ር​ሱም ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወንድምህ በአቅራቢያህ ባይኖር፣ ወይም የማን መሆኑን የማታውቅ ከሆነ፣ ባለቤቱ ፈልጎት እስኪመጣ ድረስ፣ ወደ ቤትህ ወስደህ ከአንተ ዘንድ አቈየው፤ ከዚያም መልሰህ ስጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፥ ወንድምህ እስኪፈልገው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣል፥ ለእርሱም ትመልሰዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ነገር ግን ባለቤቱ የሚኖርበት ቦታ ሩቅ ቢሆን፥ ወይም ባለቤቱ ማን እንደ ሆነ ካላወቅህ እንስሳውን ወደ ቤትህ ውሰደው፤ እርሱን ሊፈልግ በሚመጣበት ጊዜ ለባለቤቱ ስጠው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣል፥ ለእርሱም ትመልሰዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 22:2
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።


“የወ​ን​ድ​ምህ በሬ ወይም በግ በመ​ን​ገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አት​በል፤ እነ​ር​ሱን መል​ሰህ ለወ​ን​ድ​ምህ ስጥ።


አህ​ያ​ውም ቢሆን፥ በሬ​ውም ቢሆን፥ ወይም ልብሱ ቢሆን እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እን​ዲ​ሁም በወ​ን​ድ​ምህ በጠ​ፋ​በት ነገር ሁሉ ባገ​ኘ​ኸው ጊዜ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቸል ልት​ለው አይ​ገ​ባ​ህም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች