Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 20:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ለመ​ብል የማ​ይ​ሆ​ኑ​ትን የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ዛፎች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ትቈ​ር​ጣ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እስ​ክ​ታ​ሸ​ን​ፋ​ትም ድረስ በም​ት​ዋ​ጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመ​ሽ​ጋ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቀውን ዛፍ ግን ልትቈርጠውና ጦርነት የምታካሂድባትን ከተማ በድል እስክትቈጣጠራት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀምበት ትችላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቆርጣቸዋለህ፥ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ፍሬ የማያፈሩትን ሌሎች ዛፎች ግን እየቈረጥህ በመከመር ከተማይቱ እስከምትማረክበት ጊዜ ድረስ ለከበባ ተግባር ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቈርጣቸውማለህ፤ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 20:20
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ሁሉ ትመ​ታ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ት​ንም ዛፎች ሁሉ ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ትደ​ፍ​ና​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ሞ​ቹ​ንም እር​ሻ​ዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ታበ​ላ​ሻ​ላ​ችሁ።”


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በብ​ል​ሃ​ተ​ኞች እጅ የተ​ሠ​ሩ​ትን ፥ በግ​ን​ብና በቅ​ጥር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን፥ ፍላ​ጻና መርግ የሚ​ወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ውን መሣ​ሪ​ያ​ዎች አደ​ረገ፤ እስ​ኪ​በ​ረ​ታም ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ንቅ ረድ​ቶ​ታ​ልና የመ​ሣ​ሪ​ያ​ዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።


ታናሽ ከተማ ነበ​ረች፥ ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችም ነበ​ሩ​ባት፤ ታላቅ ንጉ​ሥም መጣ​ባት፥ ከበ​ባ​ትም፥ ታላቅ ግን​ብ​ንም ሠራ​ባት።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ወደ​ዚች ከተማ አይ​መ​ጣም፤ ፍላ​ጻ​ንም አይ​ወ​ረ​ው​ር​ባ​ትም፤ በጋ​ሻም አይ​መ​ጣ​ባ​ትም፥ አያ​ጥ​ራ​ት​ምም።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ሽ​ግና ለመ​ከ​ላ​ከያ ስለ ፈረ​ሱት ስለ​ዚ​ህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እን​ዲህ ይላ​ልና፦


ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ዛፎ​ች​ዋን ቍረጡ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ኀይ​ልን አፍ​ስሱ ይህች ከተማ የሐ​ሰት ከተማ ናት፤ መካ​ከ​ልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


ብዙ​ዎ​ችን ነፍ​ሳት ለማ​ስ​ወ​ገድ ምሽ​ግን በመ​ሸጉ፥ ቅጥ​ር​ንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈር​ዖን በታ​ላቅ ኀይ​ልና በብዙ ሕዝብ በጦ​ር​ነት አይ​ረ​ዳ​ውም።


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


“ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​ው​ጋ​ትና ለመ​ው​ሰድ ብዙ ቀን ብት​ከ​ብ​ባት፥ ምሳ​ር​ህን አን​ሥ​ተህ ዛፎ​ች​ዋን አት​ቍ​ረጥ፤ ከእ​ነ​ርሱ ትበ​ላ​ለ​ህና አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ አንተ ይመ​ጣና ወደ ቅጥ​ር​ህም ይገባ ዘንድ የም​ድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር የተ​ገ​ደለ ሰው በሜዳ ወድቆ ቢገኝ፥ ገዳ​ዩም ባይ​ታ​ወቅ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች