Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 16:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ጠ​ላ​ውን ሐው​ልት ለአ​ንተ አታ​ቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌታ እግዚአብሔርም የሚጠላውን የማምለኪያ ሐውልት ለአንተ አታቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ደግሞም አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠላውን የማምለኪያ የድንጋይ ምሰሶ አታቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አምላክህ እግዚአብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 16:22
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠ​ሉም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ች​ንም ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ።


በረ​ጃ​ጅሙ ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ ዐም​ዶ​ችን ተከሉ፤


“በላይ በሰ​ማይ ከአ​ለው፥ በታ​ችም በም​ድር ከአ​ለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ከአ​ለው ነገር የማ​ና​ቸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አም​ላክ አታ​ድ​ርግ።


ነገር ግን መሠ​ው​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ብ​ራ​ላ​ችሁ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ውን ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ፤


በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።


“ለእ​ና​ንተ በእጅ የተ​ሠራ ጣዖት አታ​ድ​ርጉ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸም ምስል ወይም ሐው​ልት አታ​ቁሙ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም ዘንድ በም​ድ​ራ​ችሁ ላይ የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ አታ​ኑሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፣ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፣ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።


እን​ዳ​ት​በ​ድሉ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል፥ የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ምሳሌ፥ በወ​ንድ ወይም በሴት መልክ የተ​ሠ​ራ​ውን፥ በም​ድር ላይ ያለ​ውን፥


ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን እን​ዳ​ት​ረሱ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ለ​ከ​ለ​ውን፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ተጠ​ን​ቀቁ።


“ልጆ​ችን፥ የልጅ ልጆ​ች​ንም በወ​ለ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ረዥም ዘመን በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ በበ​ደ​ላ​ች​ሁም ጊዜ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ፥ ታስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር በሠ​ራ​ችሁ ጊዜ፥


እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።


ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች