Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ሁሉ በየ​ነ​ገ​ዶ​ችህ ፈራ​ጆ​ች​ንና መባ​ውን የሚ​ጽ​ፉ​ትን ሹሙ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ቅን ፍር​ድን ይፍ​ረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በጽድቅ ፍርድ ይዳኙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “አምላክህ እግዚአብሔር ለየነገድህ በሚሰጠው ምድር በእያንዳንዱ ከተማ ዳኞችና ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ትሾማለህ፤ እነዚህም ሰዎች ለሕዝቡ ያለ አድልዎ መፍረድ ይገባቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በአገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና አለቆችን ሹም፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድ ይፍረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 16:18
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።


ከይ​ሰ​ዓ​ራ​ው​ያን ከና​ን​ያና ልጆቹ ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ይሆኑ ዘንድ በው​ጭው ሥራ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተሾ​መው ነበር።


አን​ተም ዕዝራ፥ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለው እንደ አም​ላ​ክህ ጥበብ መጠን በወ​ንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ሕግ በሚ​ያ​ውቁ ሁሉ ላይ ይፈ​ርዱ ዘንድ ጻፎ​ች​ንና ፈራ​ጆ​ችን ሹም፤ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።


አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው።


“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ ያረ​ገ​ዘ​ች​ንም ሴት ቢያ​ቈ​ስሉ ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ ያል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅን​ስም ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት፥ የሴ​ቲቱ ባል የጣ​ለ​በ​ትን ያህል ካሳ ይክ​ፈል፤


ጌታው ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጆች ይው​ሰ​ደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃ​ኑም አቅ​ርቦ አፍ​ን​ጫ​ውን በወ​ስፌ ይብ​ሳው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪ​ያው ይሁ​ነው።


“ለቀደሙት ‘አትግደል’ እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጣ​ችሁ በረ​ከት መጠን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ እንደ ችሎ​ታ​ችሁ ታመ​ጣ​ላ​ችሁ።


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤


ወደ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት በዚ​ያም ዘመን ወደ አሉ ፈራ​ጆች መጥ​ተህ ትጠ​ይ​ቃ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም የፍ​ር​ዱን ነገር ይነ​ግ​ሩ​ሃል።


ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ህና ፈራ​ጆ​ችህ ወጥ​ተው በተ​ገ​ደ​ለው ሰው ዙሪያ እስ​ካ​ሉት ከተ​ሞች ድረስ በስ​ፍር ይለኩ፤


“በሰ​ዎች መካ​ከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍር​ድም ቢመጡ፥ ቢፋ​ረ​ዱም ለጻ​ድቁ ይፈ​ረ​ድ​ለት፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ይፈ​ረ​ድ​በት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳሙ​ኤል በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልጆ​ቹን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች