Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጣ​ችሁ በረ​ከት መጠን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ እንደ ችሎ​ታ​ችሁ ታመ​ጣ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን እያንዳንዱ ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አምላክህ ጌታ በረከት እንደሰጠው መጠን እያንዳንዱ ሰው እንደ ችሎታው ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እያንዳንዱም የሚያመጣው ስጦታ እግዚአብሔር በሰጠው በረከት መጠን ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አምላክህ እግዚአብሔር በረከት እንደ ሰጠህ መጠን እያንዳንዱ ሰው እንደ ችሎታው ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 16:17
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


ለወ​ይ​ፈ​ኑም አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እንደ ቻለው ያህል፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህሉ ቍር​ባን ያቅ​ርብ።


ለግ​ምቱ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ቢያጣ ግን በካ​ህኑ ፊት ይቁም፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለ​ውን ሰው ከእጁ ባለው ገን​ዘብ መጠን ይገ​ም​ት​ለት፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለው ሰው እን​ደ​ሚ​ችል መጠን ይገ​ም​ት​ለት።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከ​ህን ያህል እጅህ መስ​ጠት በም​ት​ች​ለው መጠን ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ባ​ቱን ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።


በዓ​መት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰ​ባቱ ሱባ​ዔም በዓል፥ በዳ​ስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ይታይ፤


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ሁሉ በየ​ነ​ገ​ዶ​ችህ ፈራ​ጆ​ች​ንና መባ​ውን የሚ​ጽ​ፉ​ትን ሹሙ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ቅን ፍር​ድን ይፍ​ረዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች