Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 15:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ነው​ረኛ ወይም አን​ካሳ ወይም ዕውር ቢሆን፥ ወይም አን​ዳች ክፉ ነውር ቢኖ​ረው፥ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠ​ዋው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፣ ዐንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማንኛውም ዐይነት ከባድ ጕድለት ያለበት ከሆነ፣ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አንድ እንስሳ እንከን ያለው፥ አንካሳ ወይም ዕውር፥ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለጌታ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ነገር ግን እንስሶቹ እንከን ቢገኝባቸው ይኸውም ሽባ ወይም ዕውር ቢሆኑ፥ ወይም ደግሞ የባሰ ነውር ቢኖርባቸው፥ እነርሱን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ነውረኛ ወይም አንካሳ ወይም ዕውር ቢሆን፥ ወይም አንዳች ክፉ ነውር ቢኖረው፥ ለአምላክ ለእግዚአብሔር አትሠዋው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 15:21
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


በእ​ሳ​ትም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


“በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለ​በ​ትን በሬ ወይም በግ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠዋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች