Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 15:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ድሃ ከም​ድ​ርህ ላይ አይ​ታ​ጣ​ምና ስለ​ዚህ እኔ፦ በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ላለው ድሃ፥ ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ወን​ድ​ምህ እጅ​ህን ዘርጋ ብዬ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በምድሪቱ ላይ ድኾች ምን ጊዜም አይጠፉም፤ ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፣ ለችግረኞችና ለድኾች እጅህን እንድትዘረጋ አዝዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር፤ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፥ ለድኾችና ለችግረኖች እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር በአገርህ ለሚገኙ ድኾችና ችግረኞች ጐረቤቶችህ እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ፦ በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረው ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 15:11
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳ​ር​ፋ​ትም፤ የሕ​ዝ​ብ​ህም ድሆች ይበ​ሉ​ታል፤ እነ​ርሱ ያስ​ቀ​ሩ​ት​ንም የሜዳ እን​ስሳ ይብ​ላው። እን​ዲ​ሁም በወ​ይ​ን​ህና በወ​ይ​ራህ አድ​ርግ።


ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።


ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።


ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያ​ዣ​ውን ቢመ​ልስ፥ ፈጽ​ሞም ባይ​ቀማ፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ከል​ብሱ ቢያ​ለ​ብስ፤


ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤


ለሚለምንህ ስጥ፤ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል።


ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።


ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።


ድሆች ግን ዘወ​ትር አብ​ረ​ዋ​ችሁ አሉ፤ ዘወ​ት​ርም ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ መል​ካም ታደ​ር​ጉ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እኔን ግን ዘወ​ትር የም​ታ​ገ​ኙኝ አይ​ደ​ለም።”


መሬ​ታ​ቸ​ው​ንና ጥሪ​ታ​ቸ​ው​ንም እየ​ሸጡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ደ​ሚ​ያ​ሻው ይሰጡ ነበር።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ካሉ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ከሚ​ኖሩ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ አንዱ ቢቸ​ገር ልብ​ህን አታ​ጽና፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ከመ​ስ​ጠት እጅ​ህን አት​መ​ልስ።


ነገር ግን እጅ​ህን ለእ​ርሱ ዘርጋ፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ሁሉ ስጠው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች