Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 10:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አባ​ቶ​ችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዛ​ት​ህን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አደ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አባቶችህ ወደ ግብጽ ሲወርዱ ሰባ ነበሩ፤ አሁን ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ሰማይ ከዋክብት አብዝቶሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አባቶችህ ሰባ ሰው ሆነው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ አሁን ግን ጌታ አምላክህ ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የቀድሞ አባቶችህ ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜ ብዛታቸው ሰባ ብቻ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር አምላክህ የአንተን ቊጥር ብዛት እንደ ሰማይ ከዋክብት አድርጎታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አባቶችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁንም አምላክህ እግዚአብሔር ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 10:22
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው።


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት ሰዎች ሁሉ ከጕ​ል​በቱ የወ​ጡት፥ ከል​ጆቹ ሚስ​ቶች ሌላ፥ ሁላ​ቸው ስድሳ ሰባት ናቸው።


በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ሁለት ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገ​ቡት የያ​ዕ​ቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።


ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።


ዮሴ​ፍም አስ​ቀ​ድሞ በግ​ብፅ ነበረ። ከያ​ዕ​ቆብ ጕል​በት የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍ​ሶች ነበሩ፤


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ስድ​ስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።


ከአ​ንድ ወርም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አል​ተ​ሰ​ጣ​ቸ​ው​ምና ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


ዮሴ​ፍም አባ​ቱን ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዘመ​ዶ​ቹን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ላከ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሰባ አም​ስት ነፍስ ነበር።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ዝ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እነ​ሆም፥ እና​ንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ብዙ​ዎች ናችሁ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ቍጥር ላይ እልፍ አእ​ላ​ፋት ይጨ​ምር፤ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁም ይባ​ር​ካ​ችሁ።


በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ከብ​ዛ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት የነ​በ​ረው ቍጥ​ራ​ችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀ​ራል።


ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች