Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በእ​ርሱ ፍጹም መለ​ኮቱ በሥጋ ተገ​ልጦ ይኖ​ራ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በርሱ ይኖራልና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል ተገልጦ ይኖራልና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የአምላክነት ፍጹም ሙላት በአካል ተገልጦ የሚኖረው በክርስቶስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 2:9
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉ በእ​ርሱ ፍጹም ሆኖ ይኖር ዘንድ፥ ወዶ​አ​ልና።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


እኔና አብ አንድ ነን።”


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


ከሠ​ራሁ ግን፥ እኔን እን​ኳን ባታ​ምኑ እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ ታው​ቁና ትረዱ ዘንድ ሥራ​ዬን እመኑ።”


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ፥ እና​ን​ተም በእኔ፥ እኔም በእ​ና​ንተ እን​ዳ​ለሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ አብ በእኔ እን​ዳ​ለህ፥ እኔም በአ​ንተ እን​ዳ​ለሁ፥ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም የር​ግብ መልክ ባለው አካል አም​ሳል በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰ​ማ​ይም፥ “የም​ወ​ድህ፥ በአ​ን​ተም ደስ የሚ​ለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ብሎ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሳያ​ስብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ር​ስ​ቶስ ዓለ​ሙን ከራሱ ጋር አስ​ታ​ር​ቆ​አ​ልና፤ የዕ​ርቅ ቃሉ​ንም በእኛ ላይ አደ​ረገ፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ው​ንም መል​እ​ክት ሰጠን።


መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።


እርሱ ግን ይህን የተ​ና​ገ​ረው ቤተ መቅ​ደስ ስለ ተባለ ሰው​ነቱ ነበር።


እኛም ሁላ​ችን ከሙ​ላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀ​በ​ልን።


እን​ግ​ዲህ እኛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ዶች ከሆን በሰው ዕው​ቀ​ትና ብል​ሀት በተ​ቀ​ረጸ በድ​ን​ጋ​ይና በብር፥ በወ​ር​ቅም አም​ላ​ክ​ነ​ቱን ልን​መ​ስ​ለው አይ​ገ​ባም።


ከዚ​ህም በኋላ አገ​ል​ጋዩ፦ አቤቱ እንደ አዘ​ዝ​ኸኝ አደ​ረ​ግሁ፤ ገናም ቦታ አለ አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች