Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ምንም በሥጋ ከእናንተ ርቄ ብገኝ በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ነኝና በሥርዐት መኖራችሁንና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በአካል ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፤ መልካሙንም ሥነ ሥርዓታችሁንና በክርስቶስም ላይ ያላችሁን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በሥጋ ከእናንተ ብርቅም እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ በመልካም ሥነ ሥርዓት መኖራችሁንና በክርስቶስ ላይ ያላችሁን ጽኑ እምነት በማየትም ደስ ይለኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 2:5
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤


በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።


ትጉ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ቁሙ፤ ታገሡ ጽኑ፤


በዚች ጽድቅ እስከ መጨ​ረሻ የቀ​ደ​መ​ውን ሥር​ዐ​ታ​ች​ንን አጽ​ን​ተን ከጠ​በ​ቅን ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ሁነ​ና​ልና።


ነገር ግን ሁሉን በአ​ገ​ባ​ብና በሥ​ር​ዐት አድ​ርጉ፤


ይህ​ችም ተስፋ ነፍ​ሳ​ችን እን​ዳ​ት​ነ​ዋ​ወጥ እንደ መል​ሕቅ የም​ታ​ጸና ናት፤


እናንተ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ፥ አሁን በሕይወት እንኖራለንና።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


የቀ​ደ​መ​ውን በደ​ላ​ች​ንን አታ​ስ​ብ​ብን፥ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በቶሎ ያግ​ኘን፥ እጅግ ተቸ​ግ​ረ​ና​ልና።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ስብና ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ቀ​ር​በው የመ​ጠጥ ቍር​ባን ጋር ብዙ ነበረ። እን​ዲ​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ተዘ​ጋጀ።


ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።


መሰ​ብ​ሰ​ባ​ችሁ ለፍዳ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የተ​ራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አት​ነ​ቃ​ቀ​ፉም፤ ሌላ​ውን ሥር​ዐት ግን መጥቼ እሠ​ራ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


በሐ​ዋ​ር​ያት ትም​ህ​ር​ትና በአ​ን​ድ​ነት ማዕ​ድን በመ​ባ​ረክ፥ በጸ​ሎ​ትም ጸን​ተው ይኖሩ ነበር።


ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ በየ​ቀኑ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ መባ​ውን በቀን በቀኑ ያቅ​ርብ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች