Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዘወ​ትር ስለ እና​ንተ እና​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለ እናንተ በምንጸልይበት ጊዜ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለ እናንተ ስንጸልይ፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ለእናንተ በምንጸልይበት ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ዘወትር እናመሰግናለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-5 ስለ እናንተ ስንጸልይ፥ በሰማይ ከተዘጋጀላችሁ ተስፋ የተነሣ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ እምነታችሁ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተን፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ስለዚህም ተስፋ በወንጌል እውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 1:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ሥራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤


ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤


ስለ​ዚ​ህም እኛ ዜና​ች​ሁን ከሰ​ማን ጀምሮ፥ በፍ​ጹም ጥበ​ብና በፍ​ጹም መን​ፈ​ሳዊ ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ማወ​ቅን ትፈ​ጽሙ ዘንድ፥ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና መለ​መ​ንን አል​ተ​ው​ንም።


ስለ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለእ​ና​ንተ ስለ​ተ​ሰ​ጣ​ችሁ ጸጋ ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።


ከጨ​ለማ አገ​ዛዝ አዳ​ነን፤ ወደ ተወ​ደ​ደው ልጁ መን​ግ​ሥ​ትም መለ​ሰን።


ስለ​ዚ​ህም እኔ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ና​ች​ሁን፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ መው​ደ​ዳ​ች​ሁን ሰምቼ፥


በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ።


ሁላ​ችን አንድ ሆነን በአ​ንድ አፍ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ።


የም​ሕ​ረት አባት፥ የመ​ጽ​ና​ና​ትም ሁሉ አም​ላክ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


በጸ​ሎ​ትና በም​ልጃ ሁሉ ዘወ​ትር በመ​ን​ፈስ ጸልዩ፤ ከዚ​ህም ጋር ስለ ቅዱ​ሳን ሁሉ ለመ​ጸ​ለይ ሁል​ጊዜ ትጉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች