Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር፥ ሰውም ሳይ​ፈ​ጠር ተሰ​ውሮ የነ​በ​ረ​ውን ምክ​ሩን እፈ​ጽም ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ይህም ቃል ከዘመናትና ከትውልዶች ተሰውሮ ምስጢር ሆኖ ቈይቶ ነበር፤ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጧል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ይህም ቃል ከዘመናትና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፤ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ይህም የእግዚአብሔር ቃል ባለፉት ዘመናት ከሰው ልጆች ተሰውሮ የቈየውና አሁን ግን እግዚአብሔር ለሚያምኑት ሁሉ የገለጠው ምሥጢር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 1:26
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ፤’ አላቸው።


እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ምሥ​ጢር ማወቅ ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ለእ​ነ​ዚያ ግን አይ​ተው እን​ዳ​ያዩ፥ ሰም​ተ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም በም​ሳሌ ነው።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ከዘ​መ​ናት በፊት ለክ​ብ​ራ​ችን የወ​ሰ​ነ​ውን ተሰ​ው​ሮም የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በም​ሥ​ጢር እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው።


ስለ እርሱ የታ​ሰ​ር​ሁ​ለ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሥ​ጢር እን​ድ​ን​ና​ገር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ሉን በር ይከ​ፍ​ት​ልን ዘንድ ለእ​ኛም ደግሞ ጸል​ዩ​ልን፤ ለም​ኑ​ል​ንም፤


አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና፤ እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች