Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እና​ን​ተም ቀድሞ በአ​ሳ​ባ​ች​ሁና በክፉ ሥራ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​ያ​ች​ሁና ጠላ​ቶች ነበ​ራ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በዐሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እናንተም ከእርሱ ተለይታችሁና ክፉ በመሥራት በሐሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ትኖሩ ነበር፤ በሐሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶቹ ነበራችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21-22 እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 1:21
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆ​ና​ለሁ፤ ከዐ​መ​ፃ​ዬም ራሴን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።


ይህም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ወገ​ኖች በዐ​ሳ​ባ​ቸው ከእኔ እንደ ተለ​ዩ​በት እንደ ልባ​ቸ​ውና እንደ ርኵ​ሰ​ታ​ቸው ያስ​ታ​ቸው ዘንድ ነው።”


ሐሜ​ተ​ኞች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ጠሉ፥ ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞች፥ ትም​ክ​ሕ​ተ​ኞች፥ ክፋ​ትን የሚ​ፈ​ላ​ለጉ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም የማ​ይ​ታ​ዘዙ ናቸው።


ያን​ጊዜ ክር​ስ​ቶ​ስን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕግ የተ​ለ​ያ​ችሁ ነበ​ራ​ችሁ፤ ከተ​ስ​ፋው ሥር​ዐ​ትም እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ችሁ፤ ተስ​ፋም አል​ነ​በ​ራ​ች​ሁም፤ በዚ​ህም ዓለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር።


ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ እና​ንተ ከቅ​ዱ​ሳን ጋር ባላ​ገ​ሮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።


ልቡ​ና​ቸው የተ​ጨ​ፈነ ነው፤ በስ​ን​ፍ​ና​ቸ​ውና በድ​ን​ቍ​ር​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሕይ​ወት የተ​ለዩ ናቸው።


አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች