Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በውኑ ምድ​ሪቱ ስለ​ዚህ ነገር አት​ና​ወ​ጥ​ምን? በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖር ሁሉ አያ​ለ​ቅ​ስ​ምን? ጦር​ነት እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ እንደ ግብ​ፅም ወንዝ ይሞ​ላል፤ ደግ​ሞም ይወ​ር​ዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “በዚህ ነገር ምድር አትናወጥምን? በውስጧ የሚኖሩትስ ሁሉ አያለቅሱምን? የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይፈናጠራል፤ ተመልሶም ይወርዳል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርሷም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ አትነሳምን? እንደ ግብጽም ወንዝ ተናውጣም ዳግመኛ አትወርድምን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚህ ነገር ምድር ትናወጣለች፤ በአገሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የዓባይ ወንዝ ሞልቶ በመጒደል እንደሚናወጥ አገሪቱ በሞላ ትናወጣለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርስዋም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ሙላዋም እንደ ወንዙ ትነሣለች፥ እንደ ግብጽም ወንዝ ትነሣለች ደግሞም ትወርዳለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 8:8
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍ​ስ​ንም ይመ​ል​ሳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር የታ​መነ ነው፤ ሕፃ​ና​ት​ንም ጠቢ​ባን ያደ​ር​ጋል።


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁ​ንም በላ​ያ​ቸው ዘር​ግቶ መት​ቶ​አ​ቸ​ዋል፤ ተራ​ሮ​ችም ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ፤ ሬሳ​ቸ​ውም በመ​ን​ገድ መካ​ከል እንደ ጕድፍ ሆኖ​አል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


በሚ​ኖ​ሩ​ባት ሰዎች ክፋት ምድ​ሪቱ የም​ታ​ለ​ቅ​ሰ​ውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚ​ደ​ር​ቀው እስከ መቼ ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጻ​ሜ​ያ​ች​ንን አያ​ይም ብለ​ዋ​ልና እን​ስ​ሶ​ችና ወፎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋል።


ይህ እንደ ወንዝ የሚ​ነሣ ውኃ​ውም እንደ ወንዝ የሚ​ና​ወጥ ማን ነው?


ግብፅ እንደ ወንዝ ይነ​ሣል፤ ከባ​ሕ​ሩም እን​ደ​ሚ​ታ​ወክ ማዕ​በል ይሆ​ናል፤ እር​ሱም እን​ዲህ ብሏል፥ “እነ​ሣ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ሁሉ እከ​ድ​ና​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ንና የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።


ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት የባ​ቢ​ሎ​ንን ምድር ባድማ ያደ​ር​ጋት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐሳብ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጸን​ቶ​አ​ልና ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ታመ​መ​ችም።


የሰ​ማ​ርያ ሰዎች በቤ​ት​አ​ዌን እን​ቦሳ አጠ​ገብ ይኖ​ራሉ፤ ሕዝቡ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ክብ​ሩም ከእ​ርሱ ዘንድ ወጥ​ቶ​አ​ልና እን​ዳ​ዘ​ኑ​በት እን​ዲሁ በክ​ብሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ።


ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።


ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ርን ሁሉ ይዳ​ስ​ሳል፤ ያነ​ዋ​ው​ጣ​ታ​ልም፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ግድያ እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ ደግ​ሞም እንደ ግብፅ ወንዝ ይወ​ር​ዳል።


ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።


የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች