Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እስ​ራ​ኤ​ልን ስለ ኀጢ​አቱ በም​በ​ቀ​ል​በት ቀን የቤ​ቴ​ልን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ደግሞ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ይሰ​በ​ራሉ፤ ወደ ምድ​ርም ይወ​ድ​ቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣ የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያውም ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለ ሠሩት ኃጢአት የእስራኤልን ሕዝብ በምቀጣበት ቀን በቤትኤል የሚገኙትን መሠዊያዎች አፈራርሳለሁ፤ የመሠዊያዎቹም ቀንዶች ተሰባብረው በምድር ላይ ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፥ የመሠዊያው ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 3:14
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ​ሞም በቤ​ቴል ኮረ​ብታ የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳተ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ያሠ​ራ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገጃ፥ ይህ​ንም መሠ​ዊ​ያና መስ​ገጃ አፈ​ረሰ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱ​ንም አቃ​ጠ​ለው።


ይህም ሁሉ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ገኙ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወጥ​ተው ዐም​ዶ​ቹን ሰበሩ፤ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ች​ንም አፈ​ረሱ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አጠፉ። በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ሁሉ ደግ​ሞም በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ የነ​በ​ሩ​ትን ፈጽ​መው እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ አጠ​ፉ​አ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስ​ታ​ቸ​ውና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ተመ​ለሱ።


አሁ​ንም ሂድ፤ ይህ​ንም ሕዝብ ወደ ነገ​ር​ሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ቀን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።


“ወደ ቤቴል ገብ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን ሠራ​ችሁ፤ በጌ​ል​ገ​ላም ኀጢ​አ​ትን አበ​ዛ​ችሁ፤ በየ​ማ​ለ​ዳ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ በየ​ሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁን አቀ​ረ​ባ​ችሁ፤


የቤ​ቴ​ልም ካህን አሜ​ስ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ዐም​ፆ​ብ​ሃል፤ ምድ​ሪ​ቱም ቃሉን ሁሉ ልት​ሸ​ከም አት​ች​ልም” አለ።


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


መሳ​ቂያ የሆኑ የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መቅ​ደ​ሶች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ቤት ላይ በሰ​ይፍ እነ​ሣ​ለሁ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ሠ​ው​ያው ላይ ቆሞ አየ​ሁት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “አበ​ቦች የተ​ሳ​ሉ​ባ​ቸ​ውን ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ምታ፤ መድ​ረ​ኮ​ቹም ይና​ወ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ፤ እኔም ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ሩ​ትን በሰ​ይፍ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ ከሚ​ሸ​ሹ​ትም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጡ​ትም የሚ​ድን የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች