Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “አርባ ዓመት ሲሞ​ላ​ውም ወን​ድ​ሞ​ቹን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሊጐ​በ​ኛ​ቸው በልቡ ዐሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ሙሴ አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ሊጐበኝ በልቡ ዐሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ሙሴ አርባ ዓመት በሞላው ጊዜ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ለመጐብኘት ተነሣሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 7:23
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።


በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ እር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ሁሉ አዋጅ አስ​ነ​ገረ፤ ደግ​ሞም በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ አለ፦


የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት ይወጡ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሳ​ቸ​ውን ያነ​ሣ​ሣው ሁሉ ተነሡ።


ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


ከእ​ነ​ር​ሱም ሰው ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ልቡ እን​ዳ​ነ​ሣ​ሣው፥ መን​ፈ​ሱም እሺ እን​ዳ​ሰ​ኘው ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ለማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ ለመ​ቅ​ደስ ልብስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ አመጡ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።


ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው።


ፈር​ዖ​ን​ንም በተ​ና​ገ​ሩት ጊዜ ሙሴ ሰማ​ንያ ዓመት ሆኖት ነበር፤ አሮ​ንም ሰማ​ንያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ጳው​ሎስ በር​ና​ባ​ስን፦“እን​ግ​ዲ​ህስ እን​መ​ለ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባስ​ተ​ማ​ር​ን​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ያሉ​ትን ወን​ድ​ሞች እን​ጐ​ብ​ኛ​ቸው፤ እን​ዴት እን​ዳ​ሉም እን​ወቅ” አለው።


አንድ ግብ​ፃ​ዊም ዕብ​ራ​ዊ​ውን ሲበ​ድ​ለው አገ​ኘና ለዚያ ለተ​በ​ደ​ለው ረድቶ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ገደ​ለው በአ​ሸ​ዋም ቀበ​ረው።


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች