Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 27:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ብዙ ቀንም እያ​ዘ​ገ​ምን ሄድን፤ በጭ​ን​ቅም ወደ ቀኒ​ዶስ አን​ጻር ደረ​ስን፤ ወደ​ዚ​ያም በቀ​ጥታ ለመ​ድ​ረስ ነፋስ ቢከ​ለ​ክ​ለን በቀ​ር​ጤስ በኩል በሰ​ል​ሙና ፊት ለፊት ዐለ​ፍን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ብዙ ቀን በዝግታ እየተጓዝን ቀኒዶስ አካባቢ በጭንቅ ደረስን፤ ነፋሱም ወደ ፊት እንዳንሄድ በከለከለን ጊዜ፣ በሰልሙና አጠገብ አድርገን በቀርጤስ ተተግነን ሄድን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ብዙ ቀንም እያዘገምን ሄደን በጭንቅ ወደ ቀኒዶስ አንጻር ደረስን፤ ነፋስም ስለ ከለከለን በቀርጤስ ተተግነን በሰልሙና አንጻር ሄድን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ብዙ ቀን ቀስ እያልን ተጒዘን በብዙ ችግር ወደ ቀኒዶስ ከተማ አጠገብ ደረስን፤ ነፋሱም ወደፊት እንዳንሄድ ስለ ከለከለን በሰልሞና ርእሰ ምድር ጫፍ አጠገብ አለፍንና የቀርጤስን ደሴት ተገን አድርገን ሄድን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ብዙ ቀንም እያዘገምን ሄደን በጭንቅ ወደ ቀኒዶስ አንጻር ደረስን፤ ነፋስም ስለ ከለከለን በቀርጤስ ተተግነን በሰልሙና አንጻር ሄድን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 27:7
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከቀ​ር​ጤ​ስና ከዐ​ረ​ብም የመ​ጣን፥ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጌት​ነት በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።”


ከእ​ኛም መብል የበላ አል​ነ​በ​ረም። ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ በመ​ካ​ከል ቆመና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰም​ታ​ች​ሁኝ ቢሆን ከቀ​ር​ጤ​ስም ባት​ወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳ​ትና መከራ በዳ​ና​ችሁ ነበር።


ከዚ​ያም ወጥ​ተን ነፋስ ፊት ለፊት ነበ​ርና በቆ​ጵ​ሮስ በኩል ዐለ​ፍን።


የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፤” ብሎአል።


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች