Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 25:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ፊስ​ጦ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ እና​ን​ተም ከእኛ ጋር ያላ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ችሁ፥ ስሙ፤ አይ​ሁድ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እን​ዳ​ይ​ገ​ባው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆነ በዚህ እየ​ጮሁ የለ​መ​ኑኝ ይህ የም​ታ​ዩት ሰው እነሆ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በዚህ ጊዜ ፊስጦስ እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፤ እንዲሁም እዚህ ዐብራችሁን ያላችሁ ሁሉ፤ ይህን ሰው ታዩታላችሁ? በኢየሩሳሌምና እዚህ በቂሳርያም የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ ይህ ሰው ከእንግዲህ በሕይወት መኖር አይገባውም በማለት እየጮኹ ለመኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ፊስጦስም አለ “አግሪጳ ንጉሥ ሆይ! እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እንዲህም አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ! አይሁድ ‘ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት መኖር አይገባውም’ በማለት እየጮኹ በኢየሩሳሌምም፥ በዚህም እንዲፈረድበት የጠየቁኝ ይህ የምታዩት ሰው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ፊስጦስም አለ፦ “አግሪጳ ንጉሥ ሆይ እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 25:24
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጳ​ው​ሎ​ስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕ​ይ​ወት ሊኖር አይ​ገ​ባ​ው​ምና እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ከም​ድር አስ​ወ​ግ​ደው” እያሉ ጮሁ።


ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የወ​ረዱ አይ​ሁድ ከብ​በ​ውት ቆሙ፤ ሊረቱ በማ​ይ​ች​ሉ​በ​ትም ብዙና ከባድ ክስ ከሰ​ሱት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች