Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጳው​ሎ​ስም መልሶ፥ “አንተ የተ​ለ​ሰነ ግድ​ግዳ በሕግ ልት​ፈ​ር​ድ​ብኝ ተቀ​ም​ጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝ​ዛ​ለ​ህን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ሃል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጳውሎስም፣ “አንተ በኖራ የተለሰንህ ግድግዳ! እግዚአብሔር ደግሞ አንተን ይመታሃል፤ በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ፣ ያለ ሕግ ስላስመታኸኝ አንተ ራስህ ሕጉን ጥሰሃል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚያን ጊዜ ጳውሎስ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ! እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ሐናንያን፥ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳን የምትመስል! አንተንም እግዚአብሔር ይመታሃል! በሕግ መሠረት የእኔን ጉዳይ ልትፈርድ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እንዲመቱኝ ታዛለህን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዚያን ጊዜ ጳውሎስ፦ አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፥ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 23:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የከ​ሓ​ናም ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ቀረበ፤ ሚክ​ያ​ስ​ንም ጕን​ጩን በጥፊ መታ​ውና፥ “ምን ዓይ​ነት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው የተ​ና​ገ​ረህ?” አለው።


ደግ​ሞም ከፀ​ሐይ በታች በጻ​ድቅ ስፍራ ኃጥእ፥ በኃ​ጥ​እም ስፍራ ጻድቅ እን​ዳለ አየሁ።


“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።


“በፍ​ርድ፥ በመ​ለ​ካ​ትም፥ በመ​መ​ዘ​ንም፥ በመ​ስ​ፈ​ርም ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን በሰ​ማይ ያደ​ር​ጋል፤ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ ይመ​ሠ​ር​ታል።


ሐናም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።


“ሕጋ​ችን አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ሰማ፤ የሠ​ራ​ው​ንም ሳያ​ውቅ በሰው ይፈ​ር​ዳ​ልን?”


በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትም ጳው​ሎ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሾ​መ​ውን ሊቀ ካህ​ናት እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ?” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች