ሐዋርያት ሥራ 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በተሰበሰበውም ሕዝብ ፊት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ትምህርት ላይ ክፉ እየተናገሩ ባላመኑ ጊዜ፥ ጳውሎስ ከእነርሱ ተለየ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ይዞ ጢራኖስ በሚባል መምህር ቤት ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አንዳንዶቹ ግን ግትር በመሆን፣ ለማመን ፈቃደኞች አልነበሩም፤ የጌታንም መንገድ በገሃድ ያጥላሉ ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ትቷቸው ሄደ፤ ደቀ መዛሙርትንም ለብቻቸው ወስዶ በጢራኖስ የትምህርት አዳራሽ ውስጥ በየዕለቱ ያነጋግራቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፤ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አንዳንዶች ግን እልኸኞች በመሆን የጌታን መንገድ በሕዝቡ ፊት እየተሳደቡ አናምንም ባሉ ጊዜ ከእነርሱ ራቀ፤ አማኞችንም ለብቻቸው ወስዶ በጢራኖስ አዳራሽ በየቀኑ ያስተምር ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |