Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “በኢ​ዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብ​ኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋ​ረጃ የመ​ሰለ ዕቃ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ተይዞ ከሰ​ማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ በተመስጦ ውስጥ እያለሁ ራእይ አየሁ፤ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር፣ በአራት ማእዘን ተይዞ ከሰማይ እኔ ወደ ነበርሁበት ቦታ ሲወርድ አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “እኔ በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ ሳለሁ ተመስጬ ራእይን አየሁ፤ ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ በአራት ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “እኔ በኢዮጴ ከተማ በጸሎት ላይ ሳለሁ በተመስጦ ራእይ አየሁ፤ ያየሁትም ትልቅ የመጋረጃ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራት ማእዘን ተይዞ ከሰማይ ሲወርድና ወደ እኔ ሲመጣ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 “እኔ በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ ሳለሁ ተመስጬ ራእይን አየሁ፤ ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ በአራት ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 11:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ እጅ ወደ እኔ ተዘ​ር​ግታ ነበር፤ እነ​ሆም የመ​ጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ነበ​ረ​ባት።


እር​ሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነው” አል​ሁት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መጥ​ቶ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


“ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ልሼ በቤተ መቅ​ደስ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብኝ።


በደ​ማ​ስ​ቆም ስሙን ሐና​ንያ የሚ​ሉት አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ ጌታም በራ​እይ ተገ​ልጦ፥ “ሐና​ንያ” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነ​ሆኝ” አለ።


በኢ​ዮጴ ሀገ​ርም ጣቢታ የም​ት​ባል አን​ዲት ደቀ መዝ​ሙር ነበ​ረች፤ በት​ር​ጓ​ሜ​ውም ዶር​ቃስ ይሉ​አ​ታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እር​ስ​ዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽ​ዋ​ትም ትሰጥ ነበር።


ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።


በኢ​ዮ​ጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙ​ዎ​ችም በጌ​ታ​ችን አመኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች