Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ዮሐ​ንስ በውኃ አጠ​መቀ፤ እና​ንተ ግን እስከ ቅርብ ቀን ድረስ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ትጠ​መ​ቃ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፣ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዮሐንስ በውሃ አጠመቀ፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 1:5
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ተራ​ሮች ማርን ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ወተ​ትን ያፈ​ስ​ሳሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ያሉት ፈፋ​ዎች ሁሉ ውኃን ያጐ​ር​ፋሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ምንጭ ትፈ​ል​ቃ​ለች፤ የሰ​ኪ​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ታጠ​ጣ​ለች።


እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤


ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።


እኔ በውሃ አጠመቅኋችሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል፤” እያለ ይሰብክ ነበር።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ግን የሚ​በ​ል​ጠኝ የጫ​ማ​ውን ማሰ​ሪያ እንኳ ልፈ​ታ​ለት የማ​ይ​ገ​ባኝ ይመ​ጣል፤ እርሱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ሳ​ትም ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ቆሞ​አል።


እኔ አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ያ​ው​ቁት ስለ​ዚህ እኔ በውኃ ላጠ​ምቅ መጣሁ።”


እኔም አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን በውኃ እን​ዳ​ጠ​ምቅ የላ​ከኝ እርሱ መን​ፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀ​መ​ጥ​በት የም​ታ​የው በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ያ​ጠ​ምቅ እርሱ ነው አለኝ።


ከጴ​ጥ​ሮስ ጋር የመጡ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆኑ ምእ​መ​ናን ሁሉ ደነ​ገጡ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱስ ጸጋ በአ​ሕ​ዝብ ላይ ወር​ዶ​አ​ልና።


ጳው​ሎ​ስም፥ “ዮሐ​ንስ ከእ​ርሱ በኋላ በሚ​መ​ጣው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ያ​ምኑ እየ​ሰ​በከ የን​ስሓ ጥም​ቀ​ትን አጠ​መቀ” አላ​ቸው።


እኛ ሁላ​ች​ንም በአ​ንድ መን​ፈስ አንድ አካል ለመ​ሆን ተጠ​ም​ቀ​ናል፤ አይ​ሁድ ብን​ሆን፥ አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብን​ሆን፥ ባሪ​ያ​ዎ​ችም ብን​ሆን፥ ነጻ​ዎ​ችም ብን​ሆን ሁላ​ችን አንድ መን​ፈስ ጠጥ​ተ​ና​ልና።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች