Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ከን​ጉሥ ገበታ ሁል​ጊዜ እየ​በላ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ኖረ፤ ሁለት እግ​ሮ​ቹም ሽባ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሜምፊቦስቴም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 መፊቦሼትም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ ሁለቱም እግሮቹ ሽባ የሆኑት መፊቦሼት በንጉሡ ገበታ እየቀረበ በመመገብ የኢየሩሳሌም ነዋሪ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሜምፊቦስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር፥ ሁለት እግሩም ሽባ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 9:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው።


ንጉ​ሡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮ​ና​ታን ልጅ አለ” አለው።


ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ሚካ የተ​ባለ ታናሽ ልጅ ነበ​ረው፤ በሲ​ባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ ያገ​ለ​ግሉ ነበር።


በወ​ህ​ኒም ውስጥ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ልብስ ለወ​ጠ​ለት፥ ኢኮ​ን​ያ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁል​ጊዜ እን​ጀራ ይበላ ነበር።


ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።


እር​ሱም በእኔ በባ​ሪ​ያህ ላይ ክፉ አደ​ረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነህ፤ በፊ​ት​ህም ደስ ያሰ​ኘ​ህን አድ​ርግ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች