Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 መላ​ዋን ኤዶ​ም​ያ​ስን ይጠ​ብቁ ዘንድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ዳዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሚ​ሄ​ድ​በት ቦታ ሁሉ ጠበ​ቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ ጌታም ዳዊት በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 8:14
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”


አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”


ዳዊ​ትም እየ​በ​ረታ፥ ከፍ እያ​ለም ሄደ፤ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።


በሄ​ድ​ህ​በ​ትም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ ከፊ​ትህ አጠ​ፋሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ እን​ዳሉ እንደ ታላ​ላ​ቆቹ ስም ስም​ህን ታላቅ አደ​ረ​ግሁ።


ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊ​ትም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።


ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥


በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሹሙም እንደ ንጉሥ ነበረ።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።


እር​ሱም በጨው ሸለቆ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላ​ንም በጦ​ር​ነት ወስዶ ስም​ዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅ​ት​ኤል” ብሎ ጠራት።


በሚ​ሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ በአ​ሦ​ርም ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ አል​ተ​ገ​ዛ​ለ​ት​ምም።


በዚ​ያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።


አም​ላኬ ሆይ፥ ልመ​ና​ዬን ስማኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም አድ​ም​ጠኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች