Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱ​ንም ንጉሥ ዳዊት ከሀ​ገ​ሮች ሁሉ አም​ጥቶ ከቀ​ደ​ሰው ከወ​ር​ቁና ከብሩ ጋር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንጉሥ ዳዊትም፣ ቀድሞ ካስገበራቸው መንግሥታት ሁሉ በገባለት ብርና ወርቅ እንዳደረገው፣ እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ንጉሥ ዳዊትም ቀድሞ ካስገበራቸው መንግሥታት ሁሉ በገባለት ብርና ወርቅ እንዳደረገው እነዚህንም ለጌታ ቀደሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11-12 ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው ከኤዶም፥ ከሞአብ፥ ከዐሞን፥ ከፍልስጥኤምና ከዐማሌቅ ከወሰደው ብርና ወርቅ፥ እንዲሁም ከሀዳድዔዜር ከወሰደው ምርኮ ጋር እነዚህንም ደግሞ ለእግዚአብሔር የተለዩ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11-12 ንጉሥ ዳዊትም ካሸነፋቸው ከአሕዛብ ሁሉ ከሶርያ ከሞዓብም ከአሞንም ልጆች ከፍልስጥኤማውያንም ከአማሌቅም ከረአብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር ምርኮ ከቀደሰው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 8:11
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።


እኔም እንደ ጉል​በቴ ሁሉ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወር​ቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረ​ትን፥ እን​ጨ​ትን፥ ደግ​ሞም መረ​ግ​ድ​ንና በፈ​ርጥ የሚ​ገባ ድን​ጋ​ይን፥ የሚ​ለ​ጠፍ ድን​ጋ​ይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለ​ው​ንም ድን​ጋይ፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም ድን​ጋይ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ።


ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።


ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤


ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች