Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ለባ​ሪ​ያ​ህም ታስ​ታ​ው​ቀው ዘንድ ስለ ቃልህ ምክ​ን​ያ​ትና እንደ ልብህ አሳብ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ አደ​ረ​ግህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለ ቃልህና እንደ ልብህ ሐሳብ ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ ባሪያህም እንዲያውቀው ገልጸህለታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ስለ ቃልህና እንደ ልብህ ሐሳብ ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ አገልጋይህንም እንዲያውቀው አደረግህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ይህን ታላቅ ነገር በቃልህ መሠረትና እንደ ልብህ ፈቃድ ያደረግኸው አገልጋይህ ያውቅ ዘንድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለባሪያህም ታስታውቀው ዘንድ ስለ ቃልህ ምክንያትና እንደ ልብህ አሳብ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ አደረግህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 7:21
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ልብ​ህም ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ለእኔ አደ​ረ​ግህ።


በተ​ና​ገ​ር​ሁት አመ​ንሁ፤ እኔም እጅግ ታመ​ምሁ።


አንተ መቀ​መ​ጤ​ንና መነ​ሣ​ቴን ታው​ቃ​ለህ። የል​ቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም። እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን? አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?


አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ቸር​ነ​ቱን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳ​ኑ​ንም ያስብ ዘንድ።


በዚ​ያች ሰዓ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ደስ አለው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከዐ​ዋ​ቂ​ዎ​ችና ከአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች ሰው​ረህ ለሕ​ፃ​ናት ስለ​ገ​ለ​ጥ​ኸው አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃ​ድህ በፊ​ትህ እን​ዲሁ ሆኖ​አ​ልና።


“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ሊሆን ከተ​ጠራ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ከሶ​ስ​ቴ​ንስ፥


እንደ ወደ​ደም በእ​ርሱ የወ​ሰ​ነ​ውን፥ የፈ​ቃ​ዱን ምሥ​ጢር ገለ​ጠ​ልን።


ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር የወ​ሰ​ናት፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የፈ​ጸ​ማት፥


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።


ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባው ስለ ጽድ​ቅ​ህና ስለ ልብህ ቅን​ነት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ በሚ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በእ​ነ​ዚያ አሕ​ዛብ ኀጢ​አት ምክ​ን​ያ​ትና ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች