2 ሳሙኤል 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ዳዊትም ሜልኮልን፥ “በእግዚአብሔር ፊት ዘምሬአለሁ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ፤ እዘምራለሁም፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ከአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በእግዚአብሔር ፊት አሸብሽቤአለሁ፤ አሁንም አሸበሽባለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ያሸበሸብኩት በጌታ ፊት ነው፤ በአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በጌታ ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በጌታ ፊት አሁንም እጨፍራለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “እኔ ያሸበሸብኩት የሕዝቡ የእስራኤል መሪ ያደርገኝ ዘንድ በአባትሽና በቤተሰቡ ፈንታ ለመረጠኝ እግዚአብሔር ክብር ነው፤ አሁንም ቢሆን እርሱን ለማክበር ከመጨፈር አልገታም፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ዳዊትም ሜልኮልን፦ በእግዚአብሔር ፊት ዘፍኛለሁ፥ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |