Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አም​ጥ​ተው ዳዊት በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ በስ​ፍ​ራዋ አኖ​ሩ​አት፤ ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሳ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው፣ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከዚያም የጌታን ታቦት አምጥተው፥ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ስፍራ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የእግዚአብሔርንም ታቦት አገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ በስፍራው አኖሩት፥ ዳዊትም የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 6:17
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊት ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም አወ​ጣት። ለእ​ርሷ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ድን​ኳን አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላት ነበ​ርና።


ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር በታ​ቦቷ ፊት ሆነው፥ ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በታ​ቦቷ ፊት ሆነው ከብ​ዛት የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊ​ትም በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ሩ​አት፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ።


ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ያቀ​ር​ባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀር​ባ​ውም ድረስ የተ​ቈ​ረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥


ዳዊ​ትም ታቦቷ በም​ታ​ር​ፍ​በት ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቆ​ማ​ቸው የመ​ዘ​ም​ራን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው።


ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች