Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለን​ጉሡ ዳዊ​ትም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ቢ​ዳ​ራን ቤትና የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገ​ሩት። ዳዊ​ትም ሄዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ስታ አመ​ጣት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚህ ጊዜ፣ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የአቢዳራን ቤተ ሰውና ያለውን ሁሉ እግዚአብሔር ባረከለት” ብለው ለንጉሥ ዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት ወደዚያው ወርዶ፣ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ አመጣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚህ ጊዜ፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የዖቤድ ኤዶም ቤተሰቡና ያለውን ሁሉ ጌታ ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት ወደዚያው ወርዶ፥ የእግዚአብሔርን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ አመጣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በቃል ኪዳኑ ታቦት ምክንያት እግዚአብሔር የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና ያለውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የባረከለት መሆኑን ንጉሥ ዳዊት ሰማ፤ ስለዚህም የቃል ኪዳኑን ታቦት በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ሊወስደው በማሰብ ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዶ አወጣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንጉሡ ዳዊትም እግዚአብሔር የአቢዳራን ቤትና የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት እንደ ባረከ ሰማ። ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 6:12
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ዳዊት አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት።


ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤተ መን​ግ​ሥት ሠርቶ ከፈ​ጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ንጉሡ ሰሎ​ሞን በጽ​ዮን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


ካህ​ና​ቱም ታቦ​ቷን አነሡ፤


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አመጡ።


በመ​ጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ ሙሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ አዘ​ዛ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በት​ከ​ሻ​ቸው ላይ በመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ ተሸ​ከሙ። መባ​እና ቍር​ባ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።


ዳዊ​ትም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት በደ​ስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።


ለአ​ብ​ር​ሃም ያደ​ረ​ገ​ውን፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም የማ​ለ​ውን፤


ዖቤ​ድ​ኤ​ዶ​ምም ልጆች ነበ​ሩት፤ በኵሩ ሰማያ፥ ሁለ​ተ​ኛው ዮዛ​ባት፥ ሦስ​ተ​ኛው ኢዮ​አስ፥ አራ​ተ​ኛው ሣካር፥ አም​ስ​ተ​ኛው ናት​ና​ኤል፤


ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓሚ​ኤል፥ ሰባ​ተ​ኛው ይሳ​ኮር፥ ስም​ን​ተ​ኛው ፒላቲ ነበሩ፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ኮ​ታ​ልና።


በዚያ ጊዜም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አባ​ቶች ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች