Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም ከኬ​ብ​ሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባ​ቶ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰደ፤ ለዳ​ዊ​ትም ደግሞ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊት ከኬብሮን ከሄደ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ቁባቶችንም አስቀመጠ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊት ከኬብሮን ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ሚስቶችና ቁባቶች እንዲኖሩት አደረገ። ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወልደውለት ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፥ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 5:13
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚህ ሁሉ ከቁ​ባ​ቶቹ ልጆች በቀር የዳ​ዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕ​ማ​ርም እኅ​ታ​ቸው ነበ​ረች።


ልቡም እን​ዳ​ይ​ስት ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ርሱ አያ​ብዛ፤ ወር​ቅና ብርም ለእ​ርሱ እጅግ አያ​ብዛ።


አብ​ያም ጸና፤ ዐሥራ አራት ሚስ​ቶ​ች​ንም አገባ፤ ሃያ ሁለ​ትም ወን​ዶች ልጆ​ች​ንና ዐሥራ ስድ​ስት ሴቶች ልጆ​ችን ወለደ።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ አድ​ርጎ እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍ እን​ዳ​ደ​ረገ ዐወቀ።


ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት።


ዳዊ​ትም ደግሞ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል አኪ​ና​ሆ​ምን ወሰደ፤ ሁለ​ቱም ሚስ​ቶቹ ሆኑ​ለት።


ባለ​ጠ​ጋ​ውም እጅግ ብዙ የበ​ግና የላም መንጋ ነበ​ረው።


በኬ​ብ​ሮን ለዳ​ዊት የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። በኵሩ አም​ኖን ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዶለ​ህያ ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቢ​ግያ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች