Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የዳ​ዊ​ት​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ቤት ወሰ​ዳት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የማለለትም መንግሥትን ከሳኦል ቤት አውጥቶ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት የሰጠው ተስፋ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት መንግሥትን ከሳኦል ቤት እንደሚወስድ ተስፋ ተሰጥቶታልና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔር ለዳዊት እንደ ማለለት እንዲሁ ከእርሱ ጋር ባላደርግ እግዚአብሔር በአበኔር ይህን ያድርግበት ይህንም ይጨምርበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 3:10
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሳሙ​ኤል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ ይሆን ዘንድ የታ​መነ እንደ ሆነ ዐወቀ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከወ​ይ​ኑና ከበ​ለሱ በታች ተዘ​ል​ለው ይቀ​መጡ ነበር።


ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን የሠ​ራ​ዊት አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሕ​ዝ​ቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቍጠ​ራ​ቸው” አለው።


እኔ እን​ዲህ እመ​ክ​ር​ሃ​ለሁ፤ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ብዛ​ታ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ አን​ተም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥ​ት​ህን ዛሬ ከእ​ጅህ ቀደ​ዳት፤ ከአ​ን​ተም ለሚ​ሻል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አሳ​ልፎ ሰጣት፤


ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን ይፈ​ራው ነበ​ርና ቃልን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ለም።


አበ​ኔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ነፍ​ስ​ህም እንደ ወደ​ደች ሁሉን እን​ድ​ት​ገዛ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልሰ​ብ​ስብ” አለው። ዳዊ​ትም አበ​ኔ​ርን አሰ​ና​በ​ተው፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቃሌ እንደ ተና​ገረ አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከእ​ጅህ ነጥቆ ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ ለዳ​ዊት ሰጥ​ቶ​ታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች