Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 24:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኦር​ናም፥ “ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ወደ አገ​ል​ጋዩ ያመ​ጣው ምክ​ን​ያት ምን​ድን ነው?” አለ። ዳዊ​ትም፥ “መቅ​ሠ​ፍቱ ከሕ​ዝቡ ላይ ይከ​ለ​ከል ዘንድ አው​ድ​ማ​ውን ከአ​ንተ ገዝቼ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ልሠራ ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኦርናም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ወደ አገልጋዩ የመጣው ለምንድን ነው?” አለ። ዳዊትም መልሶ፣ “መቅሠፍቱ ከሕዝቡ እንዲከለከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንድሠራ ዐውድማህን ልገዛ ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኦርናም፥ “ንጉሥ ጌታዬ ወደ አገልጋዩ የመጣው ለምንድን ነው?” አለ። ዳዊትም፥ “መቅሠፍቱ ከሕዝቡ እንዲከለከል ለጌታ መሠዊያ እንድሠራ ዐውድማህን ልገዛ ነው” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ንጉሥ ሆይ! ስለምን ወደዚህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ዳዊትም “እግዚአብሔር የቸነፈሩን መቅሠፍት እንዲመልስ የአንተን አውድማ ለመግዛትና በዚያውም ላይ መሠዊያ ለመሥራት ነው የመጣሁት” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኦርናም፦ ጌታዬን ንጉሡን ወደ ባሪያው ያመጣው ምክንያት ምንድር ነው? አለ። ዳዊትም፦ መቅሠፍቱ ከሕዝቡ ላይ ይከለከል ዘንድ አውድማውን ከአንተ ገዝቼ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ልሠራ ነው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 24:21
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማዕ​በ​ሉም ዝም አለ፥ አር​ፈ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው። ወደ ፈለ​ጉ​ትም ወደብ መራ​ቸው።


ዳዊ​ትም ኦር​ናን፥ “በላዩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአ​ው​ድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥ​ልኝ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከሕ​ዝቤ ይከ​ለ​ከ​ላል” አለው።


በዚ​ያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣ፤ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ” አለው።


ኢዮ​አ​ብም ንጉ​ሡን፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ዐይን እያየ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨ​ም​ር​በት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈ​ል​ጋል?” አለው።


ያንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰው ተከ​ትሎ ወደ ድን​ኳኑ ገባ። ሁለ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ሰውና ምድ​ያ​ማ​ዊ​ቱን ሴት ሆዳ​ቸ​ውን ወጋ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መቅ​ሠ​ፍቱ ተወ​ገደ።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት።


ኦር​ናም ሲመ​ለ​ከት ንጉ​ሡና ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦር​ናም ወጥቶ በን​ጉሡ ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰገደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች