Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 23:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “አቤቱ፥ ይህን አደ​ርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ሰጥ​ተው የሄዱ ሰዎች ደም አይ​ደ​ለ​ምን?” ብሎ ይጠጣ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስቱ ኀያ​ላ​ንም ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “እርሱም፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላደርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” አለ፤ ዳዊትም ሊጠጣው አልፈለገም። እንግዲህ ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “እርሱም፥ ጌታ ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላደርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቆርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” ብሎ፥ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱ ኀያላን ሰዎች የፈጸሙአቸው ተግባሮች እነዚህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ውሃ ከቶ ልጠጣው አልችልም! እኔ እርሱን ብጠጣ፥ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ኀያላን ሰዎች ደም እንደ ጠጣሁ ይቈጠራል!” አለ፤ ውሃውንም መጠጣት እምቢ አለ። ዝነኞች የሆኑት ሦስቱ ኀያላን ወታደሮች የፈጸሙአቸው የጀግንነት ተግባሮች እነዚህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፥ በነፍሳቸው ደፍረው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን? ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 23:17
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ እኛስ ሁል​ጊዜ መከ​ራን ስለ​ምን እን​ቀ​በ​ላ​ለን?


እርሱም “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።


ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።


ሁል​ጊ​ዜም የተ​ገ​ረ​ፍሁ ሆንሁ፥ መሰ​ደ​ቤም በማ​ለዳ ነው።


“ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ብር​ህና ወር​ቅህ የእኔ ነው፤ ሚስ​ቶ​ች​ህና ልጆ​ች​ህም የእኔ ናቸው።”


ኢዮ​አ​ብም መልሶ፥ “ይህ ማፍ​ረ​ስና ማጥ​ፋት ከእኔ ይራቅ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው፤ አሁ​ንም በራሱ አጠ​ገብ ያለ​ውን ጦርና የው​ኃ​ውን መን​ቀል ይዘህ እን​ሂድ፤” አለው።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።


ዛብ​ሎን ነፍ​ሱን ወደ ሞት ያሳ​ለፈ ሕዝብ ነው፤ ንፍ​ታ​ሌ​ምም በሀ​ገሩ ኮረ​ብታ ላይ ነው።


ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ይህን አደ​ርግ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት ሰው እርሱ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ እንጂ፤ እና​ንተ ግን ወደ አባ​ታ​ችሁ በደ​ኅና ሂዱ።”


ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤


“ይህን አደ​ርግ ዘንድ አም​ላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለሞት አሳ​ል​ፈው አም​ጥ​ተ​ው​ታ​ልና የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ደም እጠ​ጣ​ለ​ሁን?” አለ። ስለ​ዚ​ህም ዳዊት ይጠ​ጣው ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስ​ቱም ኀያ​ላን ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች