Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በኀ​ይል የሚ​ያ​ጸ​ናኝ ኀያል እርሱ ነው፤ መን​ገ​ዴ​ንም ንጹሕ አድ​ርጎ አዘ​ጋጀ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቀና እግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቃናልኝ እግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቃና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:33
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለቴ፥ አም​ባ​ዬም፥ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነው፤


አንተ በሥ​ራህ ንጹሕ ከሆ​ንህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምን ያገ​ደ​ዋል? መን​ገ​ድ​ህ​ንስ ብታ​ቀና ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?


በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።


እንደ ሜዳ አህያ ሆንኹ፤ ሌሊት በወና ቤት እን​ዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ።


አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።


አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ። ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ።


ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ራ​ዋ​ለች፥ በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥ በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።


እኔን ለማ​ዳን ረዳ​ትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አም​ላኬ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ነ​ው​ማ​ለሁ፤ የአ​ባቴ አም​ላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እር​ሱም፥ “ጸጋዬ ይበ​ቃ​ሀል፤ ኀይ​ልስ በደዌ ያል​ቃል” አለኝ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመ​ከ​ራዬ ልመካ ወደ​ድሁ።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


አንተ ግን በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።


በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።


የሰ​ላም አም​ላክ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በእ​ና​ንተ እያ​ደ​ረገ ፈቃ​ዱን ታደ​ርጉ ዘንድ በመ​ል​ካም ሥራ ሁሉ ፍጹ​ማን ያድ​ር​ጋ​ችሁ፤ ለእ​ርሱ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች